የአማራ ክልል ገንዘብ ቢሮ ለክልል ም/ቤት ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢዎችና አባላት ስልጠና እየሰጠ ይገኛል
የአማራ ክልል ገንዘብ ቢሮ ለአማራ ክልል ም/ቤት ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢዎችና የም/ቤት አባላት በመንግስት ግዥና ፋይናንስ አስተዳደር ዙሪያ ስልጠና እየሰጠ ነው፡፡ በስልጠና መድረኩ ላይ የተገኙት የአማራ ክልል ገንዘብ ቢሮ ኃላፊ ጥላሁን መሃሪ (ዶ/ር) የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት አስተላልፈው ስልጠናው የተዘጋጀው የም/ቤት አባላት በፋይናንስ አስተዳደር ዙሪያ የሚኖራቸውን ግንዛቤ ከፍ ለማድረግ መሆኑን ገልፀዋል፡፡ መድረኩን በንግግር የከፈቱት የአማራ ክልል ም/ቤት ዋና አፈጉባኤ የተከበሩ ወ/ሮ ፋንቱ ተስፋዬ በመንግስት ግዥና ፋይናንስ አስተዳደር ዙሪያ ገንዘብ ቢሮ የስልጠና ፕሮግራም ማዘጋጀቱ የአባላቱን ግንዛቤ በማሳደግ ረገድ የጎላ ድርሻ እንዳለው ገልፀዋል፡፡ ስልጠናው ለሚቀጥሉት ሶስት ቀናት የሚሰጥ መሆኑን ከወጣው መርሃ ግብር መረዳት ተችሏል፡፡