NEWS DETAIL

News on 'ችግሮችን የሚፈታና በእውቀት ላይ የተመሰረተ ስልጠና እየተሰጠ መሆኑ ተገለፀ።'

ችግሮችን የሚፈታና በእውቀት ላይ የተመሰረተ ስልጠና እየተሰጠ መሆኑ ተገለፀ።

የክልሉ ገንዘብ ቢሮ በመንግሥት ግዥ እና ፋይናንስ አስተዳደር ዙሪያ ለክልል ምክር ቤት ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢዎች እና አባላት በእውቀት ላይ ተመስርተው የክትትል ስራዎችን ለመስራት የሚያስችል ሥልጠና እየሰጠ ነው። የክልል ም/ቤት ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢና አባላቱ የመንግሥትን የፋይናንስ አስተዳደር እና ግዥ ሥርዓቱን ተገንዝበው በክልሉ ያሉ ባለበጀት መ/ቤቶች የሚመደበውን በጀት በአግባቡና ለታለመለት አላማ መዋሉን ለመቆጣጠር እና ወጭን በተገቢው መንገድ ማስተዳደር የሚያስችል ስራዎችን ለመመዘን በሚያስችል መልኩ ሰፊ ግንዛቤ እንዲይዙና ችግሮችንም በእውቀት ላይ ተመስርተው ለመፍታት እንዲያግዝ የተዘጋጀ ስልጠና መሆኑን የክልሉ ገንዘብ ቢሮ ኃላፊ የተከበሩ ጥላሁን መሃሪ (ዶ/ር) ገልፀዋል፡፡ የክልሉ ምክር ቤት በየጊዜው የሚያጸድቀው በጀት በፈፃሚዎች በአግባቡ ለታለመለት አላማ መዋሉን፣ የአሰራር ህግን ተከትሎ እየተመራ ስለመሆኑ መገምገምና መከታተል እንዲያስችል ተጨማሪ እውቀት የፈጠረ ስልጠና ነው የሚሉ አስተያየቶችና የተለያዩ ጥያቄዎች በሰልጣኞች ተነስተው በተነሱበት አግባብ በቢሮ ኃላፊው ጥላሁን መሃሪ (ዶ/ር) ምላሽ ተሰጥቶባቸዋል፡፡ በአማራ ክልል ምክር ቤት የበጀት እና ፋይናንስ ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ የተከበሩ ወ/ሮ ሃናን አብዱ በክልሉ በገንዘብ ቢሮ ባለሙያዎች እየተሰጠ ያለውን ሥልጠና አቅምን የሚያጐለብትና የነበረውን ክፍተት በበቂ ሁኔታ ለመሙላት የተደረገ ጥረትን አድንቀው የፋይናንስ ውጤታማነት ወይም ወጪ ቆጣቢ በሆነ መንገድ ማህበረሰቡን ተጠቃሚ ለማድረግ መስራት፣ የኦዲት ግኝቶች ላይ ጠንከር ያለ የአሰራር ስርአት መዘርጋትና ተጠያቂነት እንዲኖር በማድረግ ለተቋማት የተመደበውን በጀት በአግባቡ ስራ ላይ መዋሉን መከታተልና ያለውን ውስን ሃብት ጥቅም ላይ እንዲውል ለማድረግ የተሰጠው ስልጠና በቂ ግንዛቤ አስጨብጦናል ብለዋል፡፡ ወ/ሮ ሃናን አያይዘውም በክልሉ የተመደበው ውስን ሃብት ለታለመለት አላማ እንዲውል ሁሉም የተቋማት ኃላፊዎችና የክልሉ የም/ቤት ቋሚ ኮሚቴ አባላት የበኩላቸውን ድርሻ መወጣት እንዳለባቸው ጨምረው ገልፀዋል፡፡

Recent Posts

ቢሮው የዲጂታል ሲቪል ሰርቪስ ሪፎርም ለመገንባ…
Oct. 14, 2026
አዲሱን አመት ምክንያት በማድረግ ቢሮው ድጋፍ …
Oct. 14, 2026
የ2018 በጀት ዓመት አፈፃፀም ግምገማና የ20…
Oct. 14, 2026
ቢሮዉ በ2018 በጀት ዓመት የተሻለ ለፈጸሙ ዞ…
Oct. 14, 2026
ጠንካራ ውጤታማ የሆነ ተቋምና ፈፃሚ መገንባት …
Oct. 14, 2026
#የህብረተሰብ ተሳትፎ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት በበ…
Oct. 14, 2026
አቅመ ደካሞችን አቅም በፈቀደ መጠን መደገፍ እ…
Oct. 14, 2026
በአዲሱ የግዥና ንብረት አስተዳደር መመሪያ ስል…
Oct. 14, 2026
"በ2019 ዓ.ም በክልሉ የኤሌክትሮኒክስ የመን…
Oct. 14, 2026
የመንግስት አገልግሎትና አስተዳደር ሪፎርም አፈ…
Oct. 14, 2026
ስልጠናው አቅምን የሚገነባና ክህሎትን የሚያዳብ…
Oct. 14, 2026
የትብብርና አጋርነት ፎረሙ ለቀጣይ ተነሳሽነትን…
Aug. 4, 2026
የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ከውጭ እርዳታ ጥገ…
Aug. 4, 2026
በመንግስት ግዥ ረቂቅ መመሪያ ላይ የግብአት ማ…
Aug. 4, 2026
የፕሮጀክት ሃብቶች የመንግስት የልማት እቅዶች …
Aug. 4, 2026
ፕሮግራምን መሠረት በአደረገው የበጀት አመዳደብ…
Aug. 4, 2026
ክልሉ የቻናል አንድ ፕሮግራሞችን ውጤታማ አድር…
Aug. 4, 2026
የማዕቀፍና አለምአቀፍ ግዥዎች ከፍተኛ ኢኮኖሚያ…
Aug. 4, 2026
ሴቶች በሁሉም ዘርፍ ሚናቸው የጐላ እንደሆነ ተ…
Aug. 4, 2026
የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የግዥ አፈጻጸ…
Aug. 4, 2026
የአብሮነት፣ የአንድነትና የመቻቻል ዞን እንኳን…
Aug. 4, 2026
በረቂቅ አዋጁ ላይ ብዙ ግብዓቶች ተገኝተዋል /…
Dec. 29, 2025
ውጤታማ የፋይናንስ ተቋም እንዲፈጠር ይሰራል ሲ…
Dec. 29, 2025
የማህበዊ ተጠያቂነት ፕሮግራምን በማጠናከር አገ…
Dec. 29, 2025
የልማታዊ ሴፍትኔት ፕሮግራም (PSNP) የ5 ዓ…
Dec. 29, 2025
የልማት አጋሮች ጎደሎ የሚሞሉ ብቻ ሳይኾኑ ለእ…
Dec. 29, 2025
በተባበሩት መንግስታት የልማት ፕሮግራም (UND…
Dec. 29, 2025
"በዚህ ወቅት አማራ ክልልን መደገፍ ልዩ ያደር…
Dec. 29, 2025
ቢሮው አለም አቀፍ የጸረ ሙስና ቀንን በፓናል …
Dec. 29, 2025
# The Bureau held a discussio…
Oct. 7, 2025
#A public rally is being held…
Oct. 7, 2025
Pagume 3 “Production for Sust…
Oct. 7, 2025
# The Finance Bureau announce…
Oct. 7, 2025
# Amhara National Regional St…
Oct. 7, 2025
#Civil Society Organizations …
Oct. 7, 2025
Amhara Regional State’s 2018 …
Oct. 7, 2025
በክልሉ በሰው ሰራሽና በተፈጥሮ ለደረሰው ጉዳት…
March 13, 2025
በአማራ ክልል የህዝቡን የልማት ጥያቄዎች ለመመ…
Feb. 19, 2025
# በሶስት ክልሎች ተግባራዊ የሚሆን የ33 ሚ…
Feb. 19, 2025
የአማራ ክልል ገንዘብ ቢሮ ከፕሮጀክቶች ከዕቅድ…
Feb. 19, 2025
የካፒታል ፕሮጀክቶች አፈጻጸም ችግር ያለበት ስ…
Feb. 5, 2025
የኦዲት ግኝት ያለባቸው ተቋማት እርምት እንዲወ…
Feb. 5, 2025
ተቋማት በኦዲት የተገኘባቸውን ጉድለት እንዲያር…
Feb. 5, 2025
የእርዳታና ብድር ሃብት አጠቃቀም ትኩረት ተሰ…
Feb. 5, 2025
በአማራ ክልል በጦርነቱ ምክንያት እየደረሰ ያለ…
Feb. 5, 2025
የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች በክልሉ በሰው ሰራ…
Feb. 5, 2025
የሙስና ትግሉ የሁሉንም ህብረተሰብ ርብርብ እን…
Feb. 5, 2025
ሰብዓዊ ድጋፍ ሰጭ ድርጅቶች በአማራ ክልል ለደ…
Feb. 5, 2025
በእርዳታና ብድር የሚመጣን ሃብት ለታለመለት አ…
Feb. 5, 2025
በፈፃሚ ተቋማት ላይ የተጠያቂነት ስርዓት ተግባ…
Feb. 5, 2025
የአማራ ክልል ምክር ቤት የተቋማትን ፋይናንስ …
Feb. 5, 2025
የአማራ ክልል ገንዘብ ቢሮ ለክልል ም/ቤት ቋሚ…
Feb. 5, 2025
በአማራ ክልል የሰብዓዊ ድጋፍና ሌሎች አቅርቦቶ…
Feb. 5, 2025
#ቢሮው የ2017 በጀት ዓመት የእቅድ ኦረንቴሽ…
Feb. 5, 2025
The 2017 budget program has s…
June 19, 2024