NEWS DETAIL

News on 'በአዲሱ የግዥና ንብረት አስተዳደር መመሪያ ስልጠና'

በአዲሱ የግዥና ንብረት አስተዳደር መመሪያ ስልጠና

የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ገንዘብ ቢሮ የመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት በአዲሱ የመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር አፈፃፀም መመሪያ ዙሪያ ለክልል ተቋማት የግዥ ዳይሬክተሮች፣ ቡድን መሪዎችና ባለሙያዎች ስልጠና እየሰጠ ይገኛል፡፡ በስልጠና መድረኩ የተገኙት የአብክመ ገንዘብ ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ አደራጀው ካሴ ለክልላችን የኢኮኖሚ እድገትና የልማት ግቦች መሳካት ትልቅ ሃላፊነት ወስዳችሁ ለምትሰሩ የግዥ ዘርፍ አስተባባሪዎችና ባለሙያዎች አዲሱ የመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር መመሪያ ስልጠና መስጠት አስፈላጊ መሆኑን ገልፀው በአለፉት 15 አመታት በክልላችን ሲሰራበት የቆየው የመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 179/2003 በመተካት በአዋጅ ቁጥር 306/2018 ዓ.ም የፀደቀ ሲሆን ይህንኑ አዋጅ ተከትሎ የወጣውን የመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር መመሪያ ከ2019 በጀት አመት ጀምሮ ተግባራዊ እንደሚሆን ገልፀዋል፡፡ አዲሱ የመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር መመሪያ በርካታ ማሻሻያዎች ተደርገውበት እንደፀደቀ የገለፁት ም/ቢሮ ሃላፊው አቶ አደራጀው ከአገሪቱ የኢኮኖሚ አድገት፣ የመግዛት አቅም ለውጥ እንዲሁም አለምአቀፋዊ ሁኔታዎችን ያገናዘበ እና ከቴክኖሎጅ እድገት ጋር የተጣጣመ አሰራር ተግባራዊ ለማድረግ እንዲያስች ተደርጐ የተዘጋጀ መመሪያ መሆኑን ገልፀዋል፡፡ ከዚህ ስልጠና ሁላችንም ራሳችንን በማብቃትና ለሌሎች ባለሙያዎች ግንዛቤ በመስጠት እንደተቋም ከወዲሁ የተደራጀ እቅድ በማቀድ የግዥና ንብረት አስተዳደር ስራዎችን በማዘመንና ዲጂታላይዝ በማድረግ በኤሌክትሮኒክስ የግዥ ስርዓት መተግበር፣ አዋጁ ሲሻሻል የተጠያቂነት ስርአትንም አብሮ እንዲተገበር ተደርጐ ስለተዘጋጀ ተጠያቂነትን ማስፈንና የህግ ማስከበር ስራን በመስራት፣ ግዥዎችን ስንፈጽም የህይወት ዘመን ወጭ ትንተናና የአካባቢ ጥበቃን ታሳቢ ያደረገ ግዥ በመፈፀም መስራት እንደሚገባና በመጨረሻም የአገር ውስጥ አምራቾችን እና የስራ እድል ፈጠራን የሚያበረታታ የግዥ ስርዓት በመከተል እንዲሁም የሰነዶች አያያዝና ውል አስተዳደር ስራን በማጠናከር የግዥ ስራዎቻችንን በዚህ ልክ አስበን ለመተግበር ከወዲሁ መዘጋጀት እንደሚገባም ም/ቢሮ ኃላፊው ጨምረው ገልፀዋል፡፡ እያንዳንዱ ግዥ ፈፃሚ ተቋም ግዥዎችን ሲፈጽም መረጃዎችን በሃርድና በሶፍት ኮፒ/ዲጂታላይዝ/ መረጃ በማደራጀት መያዝ አለበት ያሉት አቶ አደራጀው የፍትህ ዘርፉም በውል አስተዳደር ስርዓት ዙሪያ የግዥ ስራዎችን እንዴት መደገፍ እንዳለበት በዚህ መድረክ ውይይት የሚደረግበት ይሆናል ብለዋል፡፡ በቀጣይም 4030 ለሚሆኑ ዞን፣ ታች ወረዳና ከተሞች ድረስ ለሚገኙ የግዥና ንብረት አስተዳደር ፈፃሚ ባለሙያዎች ተመሳሳይ ስልጠናዎች እንደሚሰጡም በመድረኩ ተገልጿል፡፡ ፌስቡክ https://www.facebook.com/share/191YyDU2YK/ ዩቲዩብ http://www.youtube.com/@AmharaFinanceBureau ቴሌግራም https://t.me/AmharaBureauofFinance ዋትስአፕ https://whatsapp.com/channel/0029Vb8BHKA4SpkAKHBs6M0H ኢንስታግራም https://www.instagram.com/amhara415?igsh=MTh1Nzd3dnNpaWRxMg== ቲክቶክ https://www.tiktok.com/@amhara.finance.bureau?_r=1... ዌብሳይት http://www.amharabofec.gov.com/ ኤክስ (ትዊተር) https://twitter.com/@amhara_finance

Recent Posts

ቢሮው የዲጂታል ሲቪል ሰርቪስ ሪፎርም ለመገንባ…
Oct. 14, 2026
አዲሱን አመት ምክንያት በማድረግ ቢሮው ድጋፍ …
Oct. 14, 2026
የ2018 በጀት ዓመት አፈፃፀም ግምገማና የ20…
Oct. 14, 2026
ቢሮዉ በ2018 በጀት ዓመት የተሻለ ለፈጸሙ ዞ…
Oct. 14, 2026
ጠንካራ ውጤታማ የሆነ ተቋምና ፈፃሚ መገንባት …
Oct. 14, 2026
#የህብረተሰብ ተሳትፎ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት በበ…
Oct. 14, 2026
አቅመ ደካሞችን አቅም በፈቀደ መጠን መደገፍ እ…
Oct. 14, 2026
"በ2019 ዓ.ም በክልሉ የኤሌክትሮኒክስ የመን…
Oct. 14, 2026
የመንግስት አገልግሎትና አስተዳደር ሪፎርም አፈ…
Oct. 14, 2026
ስልጠናው አቅምን የሚገነባና ክህሎትን የሚያዳብ…
Oct. 14, 2026
የትብብርና አጋርነት ፎረሙ ለቀጣይ ተነሳሽነትን…
Aug. 4, 2026
የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ከውጭ እርዳታ ጥገ…
Aug. 4, 2026
በመንግስት ግዥ ረቂቅ መመሪያ ላይ የግብአት ማ…
Aug. 4, 2026
የፕሮጀክት ሃብቶች የመንግስት የልማት እቅዶች …
Aug. 4, 2026
ፕሮግራምን መሠረት በአደረገው የበጀት አመዳደብ…
Aug. 4, 2026
ክልሉ የቻናል አንድ ፕሮግራሞችን ውጤታማ አድር…
Aug. 4, 2026
የማዕቀፍና አለምአቀፍ ግዥዎች ከፍተኛ ኢኮኖሚያ…
Aug. 4, 2026
ሴቶች በሁሉም ዘርፍ ሚናቸው የጐላ እንደሆነ ተ…
Aug. 4, 2026
የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የግዥ አፈጻጸ…
Aug. 4, 2026
የአብሮነት፣ የአንድነትና የመቻቻል ዞን እንኳን…
Aug. 4, 2026
በረቂቅ አዋጁ ላይ ብዙ ግብዓቶች ተገኝተዋል /…
Dec. 29, 2025
ውጤታማ የፋይናንስ ተቋም እንዲፈጠር ይሰራል ሲ…
Dec. 29, 2025
የማህበዊ ተጠያቂነት ፕሮግራምን በማጠናከር አገ…
Dec. 29, 2025
የልማታዊ ሴፍትኔት ፕሮግራም (PSNP) የ5 ዓ…
Dec. 29, 2025
የልማት አጋሮች ጎደሎ የሚሞሉ ብቻ ሳይኾኑ ለእ…
Dec. 29, 2025
በተባበሩት መንግስታት የልማት ፕሮግራም (UND…
Dec. 29, 2025
"በዚህ ወቅት አማራ ክልልን መደገፍ ልዩ ያደር…
Dec. 29, 2025
ቢሮው አለም አቀፍ የጸረ ሙስና ቀንን በፓናል …
Dec. 29, 2025
# The Bureau held a discussio…
Oct. 7, 2025
#A public rally is being held…
Oct. 7, 2025
Pagume 3 “Production for Sust…
Oct. 7, 2025
# The Finance Bureau announce…
Oct. 7, 2025
# Amhara National Regional St…
Oct. 7, 2025
#Civil Society Organizations …
Oct. 7, 2025
Amhara Regional State’s 2018 …
Oct. 7, 2025
በክልሉ በሰው ሰራሽና በተፈጥሮ ለደረሰው ጉዳት…
March 13, 2025
በአማራ ክልል የህዝቡን የልማት ጥያቄዎች ለመመ…
Feb. 19, 2025
# በሶስት ክልሎች ተግባራዊ የሚሆን የ33 ሚ…
Feb. 19, 2025
የአማራ ክልል ገንዘብ ቢሮ ከፕሮጀክቶች ከዕቅድ…
Feb. 19, 2025
የካፒታል ፕሮጀክቶች አፈጻጸም ችግር ያለበት ስ…
Feb. 5, 2025
የኦዲት ግኝት ያለባቸው ተቋማት እርምት እንዲወ…
Feb. 5, 2025
ተቋማት በኦዲት የተገኘባቸውን ጉድለት እንዲያር…
Feb. 5, 2025
የእርዳታና ብድር ሃብት አጠቃቀም ትኩረት ተሰ…
Feb. 5, 2025
በአማራ ክልል በጦርነቱ ምክንያት እየደረሰ ያለ…
Feb. 5, 2025
የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች በክልሉ በሰው ሰራ…
Feb. 5, 2025
የሙስና ትግሉ የሁሉንም ህብረተሰብ ርብርብ እን…
Feb. 5, 2025
ሰብዓዊ ድጋፍ ሰጭ ድርጅቶች በአማራ ክልል ለደ…
Feb. 5, 2025
በእርዳታና ብድር የሚመጣን ሃብት ለታለመለት አ…
Feb. 5, 2025
በፈፃሚ ተቋማት ላይ የተጠያቂነት ስርዓት ተግባ…
Feb. 5, 2025
ችግሮችን የሚፈታና በእውቀት ላይ የተመሰረተ ስ…
Feb. 5, 2025
የአማራ ክልል ምክር ቤት የተቋማትን ፋይናንስ …
Feb. 5, 2025
የአማራ ክልል ገንዘብ ቢሮ ለክልል ም/ቤት ቋሚ…
Feb. 5, 2025
በአማራ ክልል የሰብዓዊ ድጋፍና ሌሎች አቅርቦቶ…
Feb. 5, 2025
#ቢሮው የ2017 በጀት ዓመት የእቅድ ኦረንቴሽ…
Feb. 5, 2025
The 2017 budget program has s…
June 19, 2024