NEWS DETAIL

News on 'በመንግስት ግዥ ረቂቅ መመሪያ ላይ የግብአት ማሰባሰብ ውይይት ተካሄደ'

በመንግስት ግዥ ረቂቅ መመሪያ ላይ የግብአት ማሰባሰብ ውይይት ተካሄደ

የአማራ ክልል ገንዘብ ቢሮ ረቂቅ ግዥ መመሪያው ዙሪያ ግብአት ለመሰብሰብ ከአጋር አካላት ጋር ውይይት አካሄደ፡፡ በውይይት መድረኩ የተገኙት የአብክመ ገንዘብ ቢሮ ም/ኃላፊ አቶ አደራጀው ካሴ የግዥ መመሪያውን ማሻሻል ያስፈለገበት ከዚህ በፊት የነበረው መመሪያ ለረጅም ጊዜ የቆየ ከመሆኑም ባሻገር አሁን ካለው የኢኮኖሚ እድገት እና የገንዘብ የመግዛት አቅምን ታሳቢ ያደረገ ነው ብለዋል፡፡ በዚህ የግብአት ማሰባሰቢያ ውይይት የተሰጠው ሙያዊ ግብዓት በጣም ጥሩ ነው ያሉት ም/ቢሮ ኃላፊው አቶ አደራጀው የምናወጣው መመሪያ ውጤታማ እና የተዋጣለት እንዲሆን ሁሉም ባለድርሻ አካላት ግብዓት ከመስጠት ባለፈ አማራጮችን ጭምር በማመላከት በተለይም ደግሞ ከፋይናንስ ዘርፍ የሚጠበቅ መሆኑን ገልፀዋል፡፡ ይህንን መመሪያ ለማሻሻል በቢሮ ደረጃ እና የቋሚ ኮሚቴዎችን ባሳተፈ አግባብ ሰፊ ስራ ተሰርቷል ያሉት አቶ አደራጀው አሁንም የፋይናንስ ተቋማትን በዋናነት በማሳተፍ ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር አስፈላጊውን ግብዓት በማሰባሰብ የተዋጣለት መመሪያ ሆኖ እንዲዘጋጅ እየሰራን ነው ብለዋል፡፡ ቀጣይም አሉ ም/ቢሮ ኃላፊው ሁሉንም የቴክኖሎጅ አማራጮች በመጠቀም ተጨማሪ ግብአት መስጠት እንደሚገባ ገልፀው ከዛሬ ጀምሮ የተሰጠውን ግብዓት የማደራጀትና የመተንተን ስራ እንደሚሰራም አስታውቀዋል፡፡ አቶ አደራጀው አክለውም ከመመሪያው ጋር አብረው የማይሄዱ እንዲሁም ከህግና አሰራር ፣ ከአዋጁ፣ ከፖሊሲው እና ከሌሎች ህጐች አንፃርም በደንብ ታይተው ረቂቁን በማሻሻልና በመጨረሻም በፍትህ አካላት ታይቶና ተመዝግቦ መመሪያ ሆኖ ይወጣል ብለዋል፡፡ ይህንን መመሪያ ተከትሎ ሌሎች መመሪያዎች በተለይም ቀላል የወረዳና የቀበሌ የግዥ መመሪያ እንዲሁም የህጋዊነት ኦዲት መመሪያና የመሳሰሉት የሚዘጋጁበት ሁኔታ እንደሚኖርም አቶ አደራጀው ጨምረው ገልፀዋል፡፡ የገንዘብ ቢሮ የቻናል አንድ ፕሮግራሞች ተወካይ አስተባባሪና የPFM ፕሮግራም አስተባባሪ ወ/ሮ ሲሃም ወርቁ በበኩላቸው ለዚህ መመሪያ በአጭር ጊዜ በዚህ ልክ የተሰጠው ግብአት ይበል የሚያስብል ነው በማለት ግዥ በባህሪው ውስብስብ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ የከተማ ግዥን ጨምሮ በአግባቡ ማየትና ይህ መመሪያ ሁሉንም ባለድርሻ አካላት እና የህብረተሰብ ክፍል ያሳተፈ እና ውጤታማ መመሪያ ሆኖ ሊዘጋጅ እንደሚገባም አሳስበዋል፡፡ የግዥ ስራችን ቀጣይ ወደ ኤሌክትሮኒክስ የግዥ ሰርአት እንደሚሸጋገርም ወ/ሮ ሲሃም ጨምረው ገልፀዋል፡፡

Recent Posts

ቢሮው የዲጂታል ሲቪል ሰርቪስ ሪፎርም ለመገንባ…
Oct. 14, 2026
አዲሱን አመት ምክንያት በማድረግ ቢሮው ድጋፍ …
Oct. 14, 2026
የ2018 በጀት ዓመት አፈፃፀም ግምገማና የ20…
Oct. 14, 2026
ቢሮዉ በ2018 በጀት ዓመት የተሻለ ለፈጸሙ ዞ…
Oct. 14, 2026
ጠንካራ ውጤታማ የሆነ ተቋምና ፈፃሚ መገንባት …
Oct. 14, 2026
#የህብረተሰብ ተሳትፎ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት በበ…
Oct. 14, 2026
አቅመ ደካሞችን አቅም በፈቀደ መጠን መደገፍ እ…
Oct. 14, 2026
በአዲሱ የግዥና ንብረት አስተዳደር መመሪያ ስል…
Oct. 14, 2026
"በ2019 ዓ.ም በክልሉ የኤሌክትሮኒክስ የመን…
Oct. 14, 2026
የመንግስት አገልግሎትና አስተዳደር ሪፎርም አፈ…
Oct. 14, 2026
ስልጠናው አቅምን የሚገነባና ክህሎትን የሚያዳብ…
Oct. 14, 2026
የትብብርና አጋርነት ፎረሙ ለቀጣይ ተነሳሽነትን…
Aug. 4, 2026
የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ከውጭ እርዳታ ጥገ…
Aug. 4, 2026
የፕሮጀክት ሃብቶች የመንግስት የልማት እቅዶች …
Aug. 4, 2026
ፕሮግራምን መሠረት በአደረገው የበጀት አመዳደብ…
Aug. 4, 2026
ክልሉ የቻናል አንድ ፕሮግራሞችን ውጤታማ አድር…
Aug. 4, 2026
የማዕቀፍና አለምአቀፍ ግዥዎች ከፍተኛ ኢኮኖሚያ…
Aug. 4, 2026
ሴቶች በሁሉም ዘርፍ ሚናቸው የጐላ እንደሆነ ተ…
Aug. 4, 2026
የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የግዥ አፈጻጸ…
Aug. 4, 2026
የአብሮነት፣ የአንድነትና የመቻቻል ዞን እንኳን…
Aug. 4, 2026
በረቂቅ አዋጁ ላይ ብዙ ግብዓቶች ተገኝተዋል /…
Dec. 29, 2025
ውጤታማ የፋይናንስ ተቋም እንዲፈጠር ይሰራል ሲ…
Dec. 29, 2025
የማህበዊ ተጠያቂነት ፕሮግራምን በማጠናከር አገ…
Dec. 29, 2025
የልማታዊ ሴፍትኔት ፕሮግራም (PSNP) የ5 ዓ…
Dec. 29, 2025
የልማት አጋሮች ጎደሎ የሚሞሉ ብቻ ሳይኾኑ ለእ…
Dec. 29, 2025
በተባበሩት መንግስታት የልማት ፕሮግራም (UND…
Dec. 29, 2025
"በዚህ ወቅት አማራ ክልልን መደገፍ ልዩ ያደር…
Dec. 29, 2025
ቢሮው አለም አቀፍ የጸረ ሙስና ቀንን በፓናል …
Dec. 29, 2025
# The Bureau held a discussio…
Oct. 7, 2025
#A public rally is being held…
Oct. 7, 2025
Pagume 3 “Production for Sust…
Oct. 7, 2025
# The Finance Bureau announce…
Oct. 7, 2025
# Amhara National Regional St…
Oct. 7, 2025
#Civil Society Organizations …
Oct. 7, 2025
Amhara Regional State’s 2018 …
Oct. 7, 2025
በክልሉ በሰው ሰራሽና በተፈጥሮ ለደረሰው ጉዳት…
March 13, 2025
በአማራ ክልል የህዝቡን የልማት ጥያቄዎች ለመመ…
Feb. 19, 2025
# በሶስት ክልሎች ተግባራዊ የሚሆን የ33 ሚ…
Feb. 19, 2025
የአማራ ክልል ገንዘብ ቢሮ ከፕሮጀክቶች ከዕቅድ…
Feb. 19, 2025
የካፒታል ፕሮጀክቶች አፈጻጸም ችግር ያለበት ስ…
Feb. 5, 2025
የኦዲት ግኝት ያለባቸው ተቋማት እርምት እንዲወ…
Feb. 5, 2025
ተቋማት በኦዲት የተገኘባቸውን ጉድለት እንዲያር…
Feb. 5, 2025
የእርዳታና ብድር ሃብት አጠቃቀም ትኩረት ተሰ…
Feb. 5, 2025
በአማራ ክልል በጦርነቱ ምክንያት እየደረሰ ያለ…
Feb. 5, 2025
የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች በክልሉ በሰው ሰራ…
Feb. 5, 2025
የሙስና ትግሉ የሁሉንም ህብረተሰብ ርብርብ እን…
Feb. 5, 2025
ሰብዓዊ ድጋፍ ሰጭ ድርጅቶች በአማራ ክልል ለደ…
Feb. 5, 2025
በእርዳታና ብድር የሚመጣን ሃብት ለታለመለት አ…
Feb. 5, 2025
በፈፃሚ ተቋማት ላይ የተጠያቂነት ስርዓት ተግባ…
Feb. 5, 2025
ችግሮችን የሚፈታና በእውቀት ላይ የተመሰረተ ስ…
Feb. 5, 2025
የአማራ ክልል ምክር ቤት የተቋማትን ፋይናንስ …
Feb. 5, 2025
የአማራ ክልል ገንዘብ ቢሮ ለክልል ም/ቤት ቋሚ…
Feb. 5, 2025
በአማራ ክልል የሰብዓዊ ድጋፍና ሌሎች አቅርቦቶ…
Feb. 5, 2025
#ቢሮው የ2017 በጀት ዓመት የእቅድ ኦረንቴሽ…
Feb. 5, 2025
The 2017 budget program has s…
June 19, 2024