የአብሮነት፣ የአንድነትና የመቻቻል ዞን እንኳን ደህና መጣችሁ //አቶ አህመድ አሊ አባፍሮ የኦሮሞ ብሄ/አስ ዞን ዋና አሰተዳዳሪ
በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የኦሮሞ ብሄ/አስ ዞን ዋና አሰተዳዳሪ የተከበሩ አቶ አህመድ አሊ አባፍሮ የ2018 በጀት ዓመት የ6 ወር አፈጻጸም ለመገምገም ለተገኙት የክልሉ ገንዘብ ቢሮ፣የዞንና ሪጆፖለታን ከተሞች ገንዘብ መምሪያዎች የአብሮነት የአንድነትና የመቻቻል ዞን ወደሆነችው የኦሮሞ ብሄ/አስ ዞን እንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር አድርገዋል፡፡ የብሄረሰብ ዞኑ ዋና አስተዳዳሪ የተከበሩ አቶ አህመድ አሊ አባፍሮ ባለፉት 4 እና 5 ዓመታት በፊት በተዘራብን ተገቢ ያልሆነ ትርክት ምክኒያት በብሄረሰብ ዞኑ በሰላም ችግር ምክኒያት የልማት የስላም እንቅስቃሴዎች ችግር እንደነበረ ገልጸው አዲሱ የብሄረሰብ ዞኑ አመራር ወንድም ከሆነው የሰሜን ሸዋ ዞን አመራር ጋር በጋራ በመተባበር በተሰራው የሰላም የልማትና የመልካም አስተዳደር ስራ አሁን ላይ ዞናችን በሰላም ፣በልማትና በብልጽግና ጎዳና ላይ እንገኛለን ብለዋል፡፡ የክልላችን መንግስት በርካታ ችግሮች ውስጥ ሆኖ አሻጋሪ የልማትና የእድገት እቅድ በማቀድ ክልሉን ለማበልጸግ እየሰራ ይገኛል ያሉት ዋና አስተዳዳሪው አቶ አህመድ አሊ አባፍሮ የቀጣይ 5 ዓመታት የስትራቴጂክ እቅድን ተግባራዊ በማድረግ የክልላችንን ልማት ለማፋጠን አንድ ብለን በጀመርንበት ወቅት የአማራ ክልል ገንዘብ ቢሮ በብሄረሰብ ዞኑ በመገኘት የ2018 በጀት ዓመት በ6 ወሩ የተፈጸሙ ዋና ዋና ተግባራትን በመገምግም የታዩ ጥንካሬዎችን በማስቀጠል፣ድክመቶችን በማስተካከልና የቀጣይ ጊዜያት ቀሪ ተግባራትን አቅጣጫ ጭምር የሜያስቀምጥበት ይሆናል ብለዋል፡፡ የፈይናንስ ተቋማት የተለያዩ የልማት ግቦችን ለማሳካት ትልቅ መሳሪያ ሆኖ እያገለገለ ያለ ተቋም ነው ያሉት ዋና አስተዳዳሪው የፋይናንስ ተቋም ትልቅ የመንግስት የጀርባ እጥንት እንደሆነም ጨምረው በመግለጽ መልካም የውይይትና የምክክር መድረክ እንዲሆን ምኞታቸውን በመግለጽ በመድረኩ መልክታቸውን አሰተላልፈዋል፡፡