አዲሱን አመት ምክንያት በማድረግ ቢሮው ድጋፍ አደረገ
የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ገንዘብ ቢሮ የ2019 አዲሱን አመት ምክንያት በማድረግ አቅመ ደካሞችን የአመት በአል መዋያ የዘይትና ፊኖ ዱቄት ድጋፍ አድርጓል፡፡ የአብክመ ገንዘብ ቢሮ ኃላፊ አቶ አታላይ ጥላሁን ድጋፍ በተደረገበት ቦታ ተገኝተው ለ2019 አዲስ አመት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት በማስተላለፍ ቢሮው የመንግስት አገልግሎትን ከመስጠት በተጨማሪ አቅመደካሞችን አቅም በፈቀደው ሁሉ የማገዝ ተግባር በየጊዜው እንደሚያደርግ ገልፀው ይህ የተደረገው ድጋፍ ከማህበረሰቡ ጐን መሆናችንን ለማሳወቅና የመተባበርና የመተጋገዝ ስሜት ለመፍጠር እንዲሁም የመረዳዳት ባህል እንዲዳብር በማሰብ መሆኑን ገልፀዋል፡፡ አቶ አታላይ አያይዘውም የበጐ ፈቃድ ተግባር በክረምት ብቻ መሆኑ ቀርቶ ድንበር ሳይኖረው አስፈላጊ በሆኑ ወቅቶች ሁሉ የሚፈፀም ተግባር ሆኖ መለመድ እንዳለበት ጨምረው ገልፀዋል፡፡ በቢሮው አካባቢ ለሚገኙ ለተመረጡ አቅመ ደካሞች ለአያንዳንዳቸው 5 ሊትር ዘይትና የ25 ኪሎ ግራም የፊኖ ዱቄት የቢሮው የማኔጅመንት አባላትና የቀበሌው አመራሮች በተገኙበት የቢሮ ኃላፊው አቶ አታላይ ጥላሁን ስጦታውን ያበረከቱ ሲሆን ባለፈው በቢሮው የተጀመሩ የ3 አቅመደካሞች ቤት ስራም በቢሮ በማኔጅመንት አባላት ተጐብኝቶ ቀሪ ስራዎች በአጭር ጊዜ ውስጥ ይጠናቀቃሉ ተብሏል፡፡ ፌስቡክ https://www.facebook.com/share/191YyDU2YK/ ዩቲዩብ http://www.youtube.com/@AmharaFinanceBureau ቴሌግራም https://t.me/AmharaBureauofFinance ዋትስአፕ https://whatsapp.com/channel/0029Vb8BHKA4SpkAKHBs6M0H ኢንስታግራም https://www.instagram.com/amhara415?igsh=MTh1Nzd3dnNpaWRxMg== ቲክቶክ https://www.tiktok.com/@amhara.finance.bureau?_r=1... ዌብሳይት http://www.amharabofec.gov.com/ ኤክስ (ትዊተር) https://twitter.com/@amhara_finance