የልማታዊ ሴፍትኔት ፕሮግራም (PSNP) የ5 ዓመት ማጠቃለያ ፕሮግራም ውይይት፡፡
የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ገንዘብ ቢሮ የፌደራል ገንዘብ ሚኒስቴር፣ የፕሮግራሙ ተጠቃሚ ክልልል ቢሮች፣ዞኖችና ወረዳዎች በተገኙበት የገጠር ልማታዊ ሴፍትኔት(PSNP) ፕሮግራም 5 ማጠቃለያና አዘጋግ ዙሪያ የአፈጻጸም ውይይት መድረክ አካሂዷል፡፡ በፕሮግራም መዝጊያ መድረኩ የተገኙት የገንዘብ ቢሮ ም/ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ መሰረት አዱኛ ክልላችን በዚህ ችግር ውስት ሆኖ የሴፍትኔት ፕሮግራምን ጨምሮ የሌሎች ፕሮግራም ስራዎችን በዚህ ልክ ውጤት በማምጣት መፈጸም መቻላችን ይበል የሚያስብል ነው ያሉ ሲሆን የፕሮግራሙ ተጠቃሚ ተቋማት ኃላፊዎች፣ፈጻሚ ባለሙያዎች ወጥታችሁ ወርዳችሁ ለአበረከታችሁት አስተዋጽኦ እና ለአስመዘገባችሁት ውጤት በቢሮው ስም ምስጋና አቀርባለሁ ብለዋል፡፡ የልማታዊ ሴፍትኔት(PSNP) 5 ፕሮግራምን በስኬት አጠናቀን ወደ ቀጣዩ ፕሮግራም ለመግባት ቀሪ ተግባራትን በፍትነት በማጠናቀቅ ምንም የሚተረፍ ሃብት ሳይኖር በውጤት በማጠናቀቅ ለህብረተሰባችን ተጠቃሚነት እንስራ ሲሉ ም/ቢሮ ኃላፊዋ ወ/ሮ መሰረት ገልጸዋል፡፡ በአፈጻጸም የተሸሉ ወረዳዎችና ዞኖች እንደፕሮግራሙ ባህሪ የምዘና ፕሮግራም ወርዶ እንዲሰራ አቅጣጫ አሰቀምተናል ያሉት ወ/ሮ መሰረት የዚህን ፕሮግራም ሂሳብ ሁሉም ዞኖችና ወረዳዎች በአግባቡ እየደገፉና ኦዲት እያደረጉ መስራት እንደሚገባም ተናግረዋል፡፡ በክልላችን የልማታዊ ሴፍትኔት ፕሮግራም አፈጻጸምን ከኛ ጋር አብሮ በመገምገም የፕሮግራሙን ስራ ለመደገፍ ለተገኙት የገንዘብ ሜኒስቴር ባልደረቦች ሁሌም ለምታደርጉልን ድጋፍ በክልሉ ስም ምስጋናችን ላቅ ያለ ነው ሲሉ ምክትል ኃላፊዋ ጨምረው ገልጸዋል፡፡ በገንዘብ ሚኒስቴር የቻናል 1 ፕሮግራሞች ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ኃለፊ አቶ ደጉ ላቀው በበኩላቸው የቻናል አንድ ፕሮግራም ለወረዳዎች የሚመደበው በጀት ከአንዳንድ ወረዳዎች መደበኛ በጀት በላይም ስለሚሆን ይህንን ሃብት በአግባቡና ለታለመለት ዓላማ ብቻ ለማዋል በኃላፊነት መስራት ይገባል ብለዋል፡፡ የውስጥ ኦዲተሮች ከ69% በላይ የፕሮግራሙን ሂሳብ ኦዲት አድርገዋል ያሉት የቻናል 1 ፐረሮግራም ማስተባበሪያ ኃላፊው አቶ ደጉ ላቀው በአጠቃላይ በክልሉ በዚህ ፕሮግራም ጥሩ ውጤት በማስመዝገብ በጥሩ ሁኔታ እየተተገበረ እንደሆነ ማየት ችያለሁ ብለዋል፡፡ አቶ ደጉ አያይዘውም ለምንሰራው ስራ ወገኔን እየረዳሁ ነው በሚል አሰተሳሰብ የሚመለከተን ሁላችንም ባለድርሻ አካላት በዘርፉ አመርቂ ስራ በመስራት የድርሻችንን እንወጣ ሲሉ አሳስበዋል፡፡