NEWS DETAIL

News on 'ጠንካራ ውጤታማ የሆነ ተቋምና ፈፃሚ መገንባት ይገባል //የአብክመ ገንዘብ ቢሮ'

ጠንካራ ውጤታማ የሆነ ተቋምና ፈፃሚ መገንባት ይገባል //የአብክመ ገንዘብ ቢሮ

የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ገንዘብ ቢሮ አዲሱን የመንግስት ግዥ እና ንብረት አስተዳደር መመሪያዎች በተመረጡ 10 ማዕከላት ለዞን፣ ለሪጅኦፖሊታን ከተሞች እና ወረዳዎች ለሚሰሩ አመራሮች፣ የግዥ ቡድን መሪዎች እና ባለሙያዎች ስልጠና ሰጥቷል፡፡ በስልጠናው ማጠቃለያ በባህር ዳር የስልጠና ማዕከል ተገኝተው በዙም ሚቲንግ ለ10ሩም ማዕከላት የማጠቃለያ ንግግር ያደረጉት የአብክመ ገንዘብ ቢሮ ኃላፊ አቶ አታላይ ጥላሁን እንደገለፁት ስልጠናው ለተከታታይ 7 ቀናት በ10 ማዕከላት ሲሰጥ እንደቆየ ገልፀው ከአሁን በፊት ለ15 አመታት ሲሰራበት የቆየው የግዥ መመሪያ በየጊዜው በበራሪ ወረቀቶች ማስተካከያዎች እየተደረጉበት ሲሰራበት የነበረ ቢሆንም ብዙ የአሰራር ክፍተቶች እንደታዩበትና ይህንን አሰራር ለማስተካከል ረጅም ጊዜ የወሰደ ከክልል እስከታች ወረዳ ድረስ ሁሉም አካላትና ሌሎች አጋርና ባለድርሻ አካላት ሁሉ ግብአት የሰጡበትና ደረጃውን የጠበቀ ሊያሰራና ለውጥ ሊያመጣ የሚችል የመንግስት ግዥ እና ንብረት አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 306/2018 ዓ.ም እና እሱን ተከትሎ የወጡ የመንግስት ግዥ አፈፃፀም መመሪያ 144/2018፣ የንብረት አስተዳደር መመሪያ 145/2018 እና ሌሎች ስተንዳርዶች እንደወጡና በነዚህ ላይ ስልጠናዎች እየተሰጡ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡ ኃላፊው አቶ አታላይ አያይዘውም የመንግስት ከፍተኛው ሃብት ወይም ከ60 እስከ 70 የሚሆነው በጀት ግዥ ላይ እንደሚውል ገልፀው ይህንን ለመፈፀም መመሪያዎች መዘጋጀታቸውን ያወሱት ኃላፊው መመሪያ መዘጋጀቱ የሪፎርም ስራ አንዱ አካል እንደሆነ እና ነገር ግን መመሪያ ማዘጋጀት ብቻ ግብአት እንዳልሆነና ይህንን መመሪያ ሊያስፈጽሙ የሚችሉ ጠንካራ ተቋም ግንባታና እያንዳንዱ ሀብት ለታለመለት አላማ እንዲውልና ወጭ ቆጣቢ በሆነ መንገድ ህግን ተከትሎ የሚፈጽም ብቁ የሰው ሃይል መፍጠርና ጠንካራ የቁጥጥር ስርአት መዘርጋት አስፈላጊ እንደሆነ ገልፀዋል፡፡ አዲሱ መመሪያ ከወጣ ለ3ኛ ዙር ስልጠና እየተሰጠ እንደሆነ የገለፁት አቶ አታላይ በቀጣይ 4030 ለሚሆኑ ሰልጣኞችም ስልጠና እንደሚሰጥ ገልፀዋል፡፡ ህግን ማሳወቅና ማስፈፀም አጣምረን በመስራት መመሪያን ባለማወቅ የሚጠየቅ እንዳይኖር ማድረግ፣ የሙያ ብቃትን ማረጋገጥ፣ ዲጂታላይዝ የሆነና የመረጃ ስርአታችን ቴክኖሎጅን በመጠቀም መተግበር፣ ንብረትን በአግባቡ ማስተዳደር እንደግዥ ሁሉ ንብረት ላይ በትኩረት መስራት፣ የተጠያቂነት ስርአት መዘርጋትና ባለቤት ሆነው እንዲሰሩ ኃላፊነት መስጠት እንደሚገባ ጨምረው ገልፀዋል፡፡ ሰልጣኞች ከዚህ ስልጠና መልስ እስከ ታች ወረዳና ቀበሌ ድረስ አጭር ስልጠና እንዲሰጡ፣ የሚነሱ ሃሳቦችን በአግባቡ በማደራጀትና በመያዝ መፍትሔ እንዲሰጣቸው እንዲደረጉ፣ የሰልጣኞችን መረጃ እንዲይዙና ጠንካራ ተቋም ለመገንባት ውጤት የሚያመጣ ተጽእኖ ፈጣሪ ባለሙያ ለመፍጠር ሁላችንም የበኩላችንን ኃላፊነት ወስደን በተግባር ውጤት የሚያመጣ ስራ መስራት አለብን ሲሉ አቶ አታላይ አቅጣጫ ሰጥተው ስልጠናውን አጠቃለዋል፡፡ ተጨማሪ መረጃዎችን ከገንዘብ ቢሮ ለማግኘት የሚከተሉትን ሊንኮች ይጠቀሙ ፌስቡክ https://www.facebook.com/share/191YyDU2YK/ ዩቲዩብ http://www.youtube.com/@AmharaFinanceBureau ቴሌግራም https://t.me/AmharaBureauofFinance ዋትስአፕ https://whatsapp.com/channel/0029Vb8BHKA4SpkAKHBs6M0H ኢንስታግራም https://www.instagram.com/amhara415?igsh=MTh1Nzd3dnNpaWRxMg== ቲክቶክ https://www.tiktok.com/@amhara.finance.bureau?_r=1... ዌብሳይት http://www.amharabofec.gov.com/ ኤክስ (ትዊተር) https://twitter.com/@amhara_finance

Recent Posts

ቢሮው የዲጂታል ሲቪል ሰርቪስ ሪፎርም ለመገንባ…
Oct. 14, 2026
አዲሱን አመት ምክንያት በማድረግ ቢሮው ድጋፍ …
Oct. 14, 2026
የ2018 በጀት ዓመት አፈፃፀም ግምገማና የ20…
Oct. 14, 2026
ቢሮዉ በ2018 በጀት ዓመት የተሻለ ለፈጸሙ ዞ…
Oct. 14, 2026
#የህብረተሰብ ተሳትፎ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት በበ…
Oct. 14, 2026
አቅመ ደካሞችን አቅም በፈቀደ መጠን መደገፍ እ…
Oct. 14, 2026
በአዲሱ የግዥና ንብረት አስተዳደር መመሪያ ስል…
Oct. 14, 2026
"በ2019 ዓ.ም በክልሉ የኤሌክትሮኒክስ የመን…
Oct. 14, 2026
የመንግስት አገልግሎትና አስተዳደር ሪፎርም አፈ…
Oct. 14, 2026
ስልጠናው አቅምን የሚገነባና ክህሎትን የሚያዳብ…
Oct. 14, 2026
የትብብርና አጋርነት ፎረሙ ለቀጣይ ተነሳሽነትን…
Aug. 4, 2026
የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ከውጭ እርዳታ ጥገ…
Aug. 4, 2026
በመንግስት ግዥ ረቂቅ መመሪያ ላይ የግብአት ማ…
Aug. 4, 2026
የፕሮጀክት ሃብቶች የመንግስት የልማት እቅዶች …
Aug. 4, 2026
ፕሮግራምን መሠረት በአደረገው የበጀት አመዳደብ…
Aug. 4, 2026
ክልሉ የቻናል አንድ ፕሮግራሞችን ውጤታማ አድር…
Aug. 4, 2026
የማዕቀፍና አለምአቀፍ ግዥዎች ከፍተኛ ኢኮኖሚያ…
Aug. 4, 2026
ሴቶች በሁሉም ዘርፍ ሚናቸው የጐላ እንደሆነ ተ…
Aug. 4, 2026
የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የግዥ አፈጻጸ…
Aug. 4, 2026
የአብሮነት፣ የአንድነትና የመቻቻል ዞን እንኳን…
Aug. 4, 2026
በረቂቅ አዋጁ ላይ ብዙ ግብዓቶች ተገኝተዋል /…
Dec. 29, 2025
ውጤታማ የፋይናንስ ተቋም እንዲፈጠር ይሰራል ሲ…
Dec. 29, 2025
የማህበዊ ተጠያቂነት ፕሮግራምን በማጠናከር አገ…
Dec. 29, 2025
የልማታዊ ሴፍትኔት ፕሮግራም (PSNP) የ5 ዓ…
Dec. 29, 2025
የልማት አጋሮች ጎደሎ የሚሞሉ ብቻ ሳይኾኑ ለእ…
Dec. 29, 2025
በተባበሩት መንግስታት የልማት ፕሮግራም (UND…
Dec. 29, 2025
"በዚህ ወቅት አማራ ክልልን መደገፍ ልዩ ያደር…
Dec. 29, 2025
ቢሮው አለም አቀፍ የጸረ ሙስና ቀንን በፓናል …
Dec. 29, 2025
# The Bureau held a discussio…
Oct. 7, 2025
#A public rally is being held…
Oct. 7, 2025
Pagume 3 “Production for Sust…
Oct. 7, 2025
# The Finance Bureau announce…
Oct. 7, 2025
# Amhara National Regional St…
Oct. 7, 2025
#Civil Society Organizations …
Oct. 7, 2025
Amhara Regional State’s 2018 …
Oct. 7, 2025
በክልሉ በሰው ሰራሽና በተፈጥሮ ለደረሰው ጉዳት…
March 13, 2025
በአማራ ክልል የህዝቡን የልማት ጥያቄዎች ለመመ…
Feb. 19, 2025
# በሶስት ክልሎች ተግባራዊ የሚሆን የ33 ሚ…
Feb. 19, 2025
የአማራ ክልል ገንዘብ ቢሮ ከፕሮጀክቶች ከዕቅድ…
Feb. 19, 2025
የካፒታል ፕሮጀክቶች አፈጻጸም ችግር ያለበት ስ…
Feb. 5, 2025
የኦዲት ግኝት ያለባቸው ተቋማት እርምት እንዲወ…
Feb. 5, 2025
ተቋማት በኦዲት የተገኘባቸውን ጉድለት እንዲያር…
Feb. 5, 2025
የእርዳታና ብድር ሃብት አጠቃቀም ትኩረት ተሰ…
Feb. 5, 2025
በአማራ ክልል በጦርነቱ ምክንያት እየደረሰ ያለ…
Feb. 5, 2025
የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች በክልሉ በሰው ሰራ…
Feb. 5, 2025
የሙስና ትግሉ የሁሉንም ህብረተሰብ ርብርብ እን…
Feb. 5, 2025
ሰብዓዊ ድጋፍ ሰጭ ድርጅቶች በአማራ ክልል ለደ…
Feb. 5, 2025
በእርዳታና ብድር የሚመጣን ሃብት ለታለመለት አ…
Feb. 5, 2025
በፈፃሚ ተቋማት ላይ የተጠያቂነት ስርዓት ተግባ…
Feb. 5, 2025
ችግሮችን የሚፈታና በእውቀት ላይ የተመሰረተ ስ…
Feb. 5, 2025
የአማራ ክልል ምክር ቤት የተቋማትን ፋይናንስ …
Feb. 5, 2025
የአማራ ክልል ገንዘብ ቢሮ ለክልል ም/ቤት ቋሚ…
Feb. 5, 2025
በአማራ ክልል የሰብዓዊ ድጋፍና ሌሎች አቅርቦቶ…
Feb. 5, 2025
#ቢሮው የ2017 በጀት ዓመት የእቅድ ኦረንቴሽ…
Feb. 5, 2025
The 2017 budget program has s…
June 19, 2024