የ2018 በጀት ዓመት አፈፃፀም ግምገማና የ2019 እቅድ ትውውቅ
የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ገንዘብ ቢሮ ከአመራሮችና ጠቅላላ ሠራተኞች ጋር የ2018 በጀት አመት እቅድ አፈፃፀም እና የ2019 እቅድ ትውውቅ መድረክ አካሄደ፡፡ በመድረኩ የተገኙት የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ገንዘብ ቢሮ ኃላፊ አቶ አታላይ ጥላሁን በ2018 በጀት አመት ቢሮው የህግ ማዕቀፎችን በማሻሻልና ለአሰራር ምቹ ሁኔታ በመፍጠር፣ የመንግስት በጀትን ወጭና ገቢ በማጣጣምና በአግባቡ በማስተዳደር እንዲሁም የእርዳታና ብድር ሃብትን ለታለመለት አላማ በማዋልና በሌሎችም ዘርፎች በጥንካሬ የሚገለፁ ስራዎች መኖራቸውን ጠቅሰው አንዳንድ ክፍተቶችን ደግሞ በማንሳት በቀጣይ ትኩረት ተሰጥቶ እንዲሰራባቸው ተናግረዋል፡፡ በሌላ በኩል ቢሮው ወደ ሪፎርም ስራ ገብቶ የትግበራ ምዕራፍ ስራ እየሰራ እንደሆነ ገልፀው ይህ ለፍፃሜ እንዲደርስ የቀሩ ተግባራትን ለይቶ በመያዝና በመፈፀም በየደረጃው ያለ አመራርና የትግበራ ኮሚቴዎችና ሁሉም ሠራተኛ በየሙያው የበኩላችንን ድርሻ በመወጣት ለፍፃሜ ማብቃት እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡ የቢሮው የ2018 በጀት አመት እቅድ አፈፃፀምና የ2019 አቅድ በቢሮው የእቅድ ዝግጅትና ክትትል ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር በአቶ መልካሙ ውበት ቀርቦ ውይይት ተካሄዶበታል፡፡ በውይይቱ የተለያዩ ሃሳቦች የተነሱና አስተያየቶች የተሰጡ ሲሆን ለሁሉም ዳይሬክቶሬቶች የቀጣይ የ2019 እቅድን ለማስፈፀም የስራ አቅጣጫ በቢሮ ኃላፊው በአቶ አታላይ ጥላሁን ተሰጥቶ ውይይቱ ተጠናቋል፡፡ በመጨረሻም የተሻለ አፈፃፀም ለነበራቸው የቢሮው ባለሙያዎች የምስጋናና የእውቅና የምስክር ወረቀት በቢሮ ኃላፊው በኩል ተበርክቶላቸዋል፡፡ ፌስቡክ https://www.facebook.com/share/191YyDU2YK/ ዩቲዩብ http://www.youtube.com/@AmharaFinanceBureau ቴሌግራም https://t.me/AmharaBureauofFinance ዋትስአፕ https://whatsapp.com/channel/0029Vb8BHKA4SpkAKHBs6M0H ኢንስታግራም https://www.instagram.com/amhara415?igsh=MTh1Nzd3dnNpaWRxMg== ቲክቶክ https://www.tiktok.com/@amhara.finance.bureau?_r=1... ዌብሳይት http://www.amharabofec.gov.com/ ኤክስ (ትዊተር) https://twitter.com/@amhara_finance