NEWS DETAIL

News on 'የልማት አጋሮች ጎደሎ የሚሞሉ ብቻ ሳይኾኑ ለእውቀት እና ለቴክኖሎጂ ሽግግር ተሳትፏቸው የጎላ …'

የልማት አጋሮች ጎደሎ የሚሞሉ ብቻ ሳይኾኑ ለእውቀት እና ለቴክኖሎጂ ሽግግር ተሳትፏቸው የጎላ ነው።

ባሕር ዳር: ታኅሣሥ 08/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል መንግሥት እና ወርልድ ቪዥን ኢትዮጵያ በቀጣይ አምስት ዓመታት የሚተገበር የልማት መርሐ ግብር ስምምነት ተፈራርመዋል። በፊርማ ሥነ ሥርዓቱ ላይ የተገኙት የአማራ ክልል ገንዘብ ቢሮ ኀላፊ አታላይ ጥላሁን የልማት አጋሮች በክልሉ ውስጥ በልማት፣ በሰላም፣ በዴሞክራሲ ግንባታ እና በአስቸኳይ ጊዜ ድጋፍ እንዲሳተፉ ምቹ ሁኔታዎች መፈጠሩን አብራርተዋል። በተለይም የልማት አጋሮች የፕሮጀክት ሀሳባቸውን ይዘው ወደ ክልሉ ሲመጡ ከክልሉ ፍላጎት ጋር ተጣጥመው እንዲሄዱ የሚያስችሉ አሠራሮች ተዘርግተዋል ነው ያሉት። የወርልድ ቪዥን ኢትዮጵያ በክልሉ ከአሁን በፊትም በጤና፣ በትምህርት፣ በንጹህ መጠጥ ውኃ፣ በጾታ እኩልነት፣ በአካባቢ ጥበቃ፣ በግብርና፣ በእንስሳት ሀብት ልማት እና በሰላም ግንባታ ዘርፎች ትኩረት አድርገው ሲሠሩ መቆየታቸውን አንስተዋል። በዚህም በርካታ ለውጦች መጥተዋል ነው ያሉት። ልማት የሁሉንም ተሳትፎ የሚጠይቅ ነው ያሉት ቢሮ ኀላፊው የልማት አጋሮች ጎደሎ የሚሞሉ ብቻ ሳይኾኑ የእውቀት እና የቴክኖሎጂ ሽግግር በማድረግ በሰው ኀይል ግንባታ እና የማኅበራዊ መሠረተ ልማቶችን በማገዝ በኩል ተሳትፏቸው የጎላ ነው ብለዋል። ዛሬ የተፈረመው የትብብር ስምምነትም እስከ ታች ድረስ ውጤታማ ለማድረግ መግባባት ላይ የተደረሠበት ነው ብለዋል። ከሚመለከታቸው ተቋማት ጋርም የጋራ የተደረገበት ስለመኾኑም ነው የጠቆሙት። በወርልድ ቪዥን ኢትዮጵያ የአማራ ክልል ፕሮግራም አስተባባሪ ቴዎድሮስ አባተ ስምምነቱ በክልሉ ከ2 ነጥብ 8 ሚሊዮን በላይ የሚኾኑ የማኅበረሰብ ክፍሎችን በቀጥታ ተጠቃሚ ያደርጋል ብለዋል። መርሐ ግብሩን በውጤታማነት ተግባራዊ ለማድረግ መንግሥት ምቹ ሁኔታዎችን በመፍጠር በአጋርነት መሥራት እንደሚገባ አንስተዋል። በተለይም መርሐ ግብሩ በሚፈጸምባቸው ወረዳዎች ማኅበረሰቡን በማንቀሳቀስ በትብብር መሥራት ይጠበቃል ነው ያሉት። የልማቱ ተጠቃሚው ማኅበረሰብም በንቃት በመሳተፍ በባለቤትነት መተባበር እንደሚያስፈልግ ጠቁመዋል። የወርልድ ቪዥን ኢትዮጵያ ብሔራዊ ዳይሬክተር ካርመን ቲል በአማራ ክልል በሰብአዊ እና በማኅበራዊ ልማት እየተሳተፉ እንደሚገኙ ጠቁመዋል። ዛሬ ከክልሉ መንግሥት ጋር የተደረገው የመግባቢያ ስምምነት በሕጻናት ጥበቃ፣ በሥነ ምግብ እና በትምህርት ላይ በዋናነት ያተኮረ ነው ብለዋል። ይህ ደግም ከሰብዓዊ ድጋፍ ባለፈ ማኅበረሰቡን በዘላቂነት በማጠናከር የተሻለ ሕይወት እንዲኖራቸው የሚያስችል ሥራ ይሠራል ነው ያሉት። ተፈጻሚ በሚኾኑት ዝርዝር ፕሮጀክቶችም ከሚመለከታቸው ቢሮዎች ጋር የጋራ ስምምነት በማድረግ ወደ ተግባር እንደሚገባ ጠቁመዋል።

Recent Posts

ቢሮው የዲጂታል ሲቪል ሰርቪስ ሪፎርም ለመገንባ…
Oct. 14, 2026
አዲሱን አመት ምክንያት በማድረግ ቢሮው ድጋፍ …
Oct. 14, 2026
የ2018 በጀት ዓመት አፈፃፀም ግምገማና የ20…
Oct. 14, 2026
ቢሮዉ በ2018 በጀት ዓመት የተሻለ ለፈጸሙ ዞ…
Oct. 14, 2026
ጠንካራ ውጤታማ የሆነ ተቋምና ፈፃሚ መገንባት …
Oct. 14, 2026
#የህብረተሰብ ተሳትፎ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት በበ…
Oct. 14, 2026
አቅመ ደካሞችን አቅም በፈቀደ መጠን መደገፍ እ…
Oct. 14, 2026
በአዲሱ የግዥና ንብረት አስተዳደር መመሪያ ስል…
Oct. 14, 2026
"በ2019 ዓ.ም በክልሉ የኤሌክትሮኒክስ የመን…
Oct. 14, 2026
የመንግስት አገልግሎትና አስተዳደር ሪፎርም አፈ…
Oct. 14, 2026
ስልጠናው አቅምን የሚገነባና ክህሎትን የሚያዳብ…
Oct. 14, 2026
የትብብርና አጋርነት ፎረሙ ለቀጣይ ተነሳሽነትን…
Aug. 4, 2026
የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ከውጭ እርዳታ ጥገ…
Aug. 4, 2026
በመንግስት ግዥ ረቂቅ መመሪያ ላይ የግብአት ማ…
Aug. 4, 2026
የፕሮጀክት ሃብቶች የመንግስት የልማት እቅዶች …
Aug. 4, 2026
ፕሮግራምን መሠረት በአደረገው የበጀት አመዳደብ…
Aug. 4, 2026
ክልሉ የቻናል አንድ ፕሮግራሞችን ውጤታማ አድር…
Aug. 4, 2026
የማዕቀፍና አለምአቀፍ ግዥዎች ከፍተኛ ኢኮኖሚያ…
Aug. 4, 2026
ሴቶች በሁሉም ዘርፍ ሚናቸው የጐላ እንደሆነ ተ…
Aug. 4, 2026
የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የግዥ አፈጻጸ…
Aug. 4, 2026
የአብሮነት፣ የአንድነትና የመቻቻል ዞን እንኳን…
Aug. 4, 2026
በረቂቅ አዋጁ ላይ ብዙ ግብዓቶች ተገኝተዋል /…
Dec. 29, 2025
ውጤታማ የፋይናንስ ተቋም እንዲፈጠር ይሰራል ሲ…
Dec. 29, 2025
የማህበዊ ተጠያቂነት ፕሮግራምን በማጠናከር አገ…
Dec. 29, 2025
የልማታዊ ሴፍትኔት ፕሮግራም (PSNP) የ5 ዓ…
Dec. 29, 2025
በተባበሩት መንግስታት የልማት ፕሮግራም (UND…
Dec. 29, 2025
"በዚህ ወቅት አማራ ክልልን መደገፍ ልዩ ያደር…
Dec. 29, 2025
ቢሮው አለም አቀፍ የጸረ ሙስና ቀንን በፓናል …
Dec. 29, 2025
# The Bureau held a discussio…
Oct. 7, 2025
#A public rally is being held…
Oct. 7, 2025
Pagume 3 “Production for Sust…
Oct. 7, 2025
# The Finance Bureau announce…
Oct. 7, 2025
# Amhara National Regional St…
Oct. 7, 2025
#Civil Society Organizations …
Oct. 7, 2025
Amhara Regional State’s 2018 …
Oct. 7, 2025
በክልሉ በሰው ሰራሽና በተፈጥሮ ለደረሰው ጉዳት…
March 13, 2025
በአማራ ክልል የህዝቡን የልማት ጥያቄዎች ለመመ…
Feb. 19, 2025
# በሶስት ክልሎች ተግባራዊ የሚሆን የ33 ሚ…
Feb. 19, 2025
የአማራ ክልል ገንዘብ ቢሮ ከፕሮጀክቶች ከዕቅድ…
Feb. 19, 2025
የካፒታል ፕሮጀክቶች አፈጻጸም ችግር ያለበት ስ…
Feb. 5, 2025
የኦዲት ግኝት ያለባቸው ተቋማት እርምት እንዲወ…
Feb. 5, 2025
ተቋማት በኦዲት የተገኘባቸውን ጉድለት እንዲያር…
Feb. 5, 2025
የእርዳታና ብድር ሃብት አጠቃቀም ትኩረት ተሰ…
Feb. 5, 2025
በአማራ ክልል በጦርነቱ ምክንያት እየደረሰ ያለ…
Feb. 5, 2025
የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች በክልሉ በሰው ሰራ…
Feb. 5, 2025
የሙስና ትግሉ የሁሉንም ህብረተሰብ ርብርብ እን…
Feb. 5, 2025
ሰብዓዊ ድጋፍ ሰጭ ድርጅቶች በአማራ ክልል ለደ…
Feb. 5, 2025
በእርዳታና ብድር የሚመጣን ሃብት ለታለመለት አ…
Feb. 5, 2025
በፈፃሚ ተቋማት ላይ የተጠያቂነት ስርዓት ተግባ…
Feb. 5, 2025
ችግሮችን የሚፈታና በእውቀት ላይ የተመሰረተ ስ…
Feb. 5, 2025
የአማራ ክልል ምክር ቤት የተቋማትን ፋይናንስ …
Feb. 5, 2025
የአማራ ክልል ገንዘብ ቢሮ ለክልል ም/ቤት ቋሚ…
Feb. 5, 2025
በአማራ ክልል የሰብዓዊ ድጋፍና ሌሎች አቅርቦቶ…
Feb. 5, 2025
#ቢሮው የ2017 በጀት ዓመት የእቅድ ኦረንቴሽ…
Feb. 5, 2025
The 2017 budget program has s…
June 19, 2024