ቢሮዉ በ2018 በጀት ዓመት የተሻለ ለፈጸሙ ዞኖች እና ከተማ አስተዳደር ገንዘብ መምሪያዎች እዉቅና ሰጠ
የአማራ ክልል ገንዘብ ቢሮ የ2018 እቅድ አፈጻጸም እና የ2019 በጀት ዓመት እቅድ ትዉዉቅ መድረክ አካሂዷል፡፡ በመድረኩ በ2018 በጀት አመት አፈፃፀም የተሻለ ለፈፀሙ የዞንና ሪጆፖሊታን ከተማ አስተዳደር ገንዘብ መምሪያዎች የእውቅና ሰርተፊኬትና የገንዘብ ሽልማት አበርክቶላቸዋል፡፡ በዚህ መሰረት ከዞን ገንዘብ መምሪያዎች ደቡብ ወሎ ዞን፣ ሰሜን ሽዋ ዞንና ማእከላዊ ጎንደር ዞን ከአንደኛ እስከ ሶስተኛ በቅደም ተከተል ወጥተው የሰርተፊኬትና የገንዘብ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል፡፡ በተመሳሳይ ከከተሞች ኮምቦልቻ ከተማ፣ ደሴ ከተማና ደብረታቦር ከተማ አስተዳደር ገንዘብ መምሪያዎች ከአንደኛ እስከ ሶስተኛ በቅደም ተከተል ወጥተው የሰርተፊኬትና የገንዘብ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል፡፡ የወልቃይት ጠገዴ ሴቴት ሁመራ ዞን ገንዘብ መምሪያ የአመቱ ልዩ ተሸላሚ በመሆን የሰርተፊኬትና ዴስክቶፕ ኮምፒዩተር ሽልማት ተበርክቶለታል፡፡ የደቡብ ወሎ ዞንና ኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ መምሪያዎች ከሰርተፊኬትና ገንዘብ ሽልማት በተጨማሪ የዋንጫ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል፡፡ ተጨማሪ መረጃዎችን ከገንዘብ ቢሮ ለማግኘት የሚከተሉትን ሊንኮች ይጠቀሙ Facebook https://www.facebook.com/AmharaBoFEC Website https://www.amharabofec.gov.et Twitter https://twitter.com/@amhara_finance YouTube https://www.youtube.com/@amharafinancebureau6403 Telegram https://t.me/AmharaBureauofFinance WhatsAPP https://chat.whatsapp.com/IyZb21gjQB6I7N3I3XFQbq TikTok https://tiktok.com/@amhara.finance.bureau