በተባበሩት መንግስታት የልማት ፕሮግራም (UNDP) የገንዘብ ድጋፍ ውጤታማ ስራዎች መከናወናቸው ተገለፀ፡፡
የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ገንዘብ ቢሮ በተባበሩት መንግስታት የልማት ፕሮግራም በUNDP የገንዘብ ድጋፍ ከሚከናወኑ ፕሮጀክቶች መካከል የ regional engagement ፕሮጀክት አንዱ ሲሆን የፕሮጀክቱ የ2025 ዕቅድ አፈፃፀም ግምገማ የፈፃሚ ቢሮ ኃላፊዎች እና የሚመለከታቸው ባለሙያዎች በተገኙበት ገምግሟል በመድረኩ የተገኙት የአብክመ ገንዘብ ቢሮ ኃላፊ አቶ አታላይ ጥላሁን በተባበሩት መንግስታት የልማት ፕሮግራም ስራዎች ዙሪያ በአቅም ግንባታ፣ስትራቴጂካዊ ጉዳዮችን ለይቶ በመደገፍ፣ በወጣቶች ስራ ፈጠራ፣ ተፈናቃይ ወገኖችን በመደገፍ እና በሌሎች ዘርፎች አበረታች ስራዎች መከናወናቸውን ገልጸዋል፡፡ ከልማት አጋሮች የሚገኙ ሃብቶችን ለተባለላቸው አላማ በማዋል የህብረተሰቡን ችግሮች በዘላቂነት ለመፍታት ጥራት ያለው ዕቅድ አቅዶ ወደ ስራ መግባት እንደሚያስፈልግም ቢሮ ኃላፊው አቶ አታላይ በግምገማ መድረኩ አንስተዋል፡፡ የገንዘብ ቢሮ የውጭ ሃብት ማስተባበሪያ ዳይሬክተሯ ወ/ሮ ሰብለወርቅ ሙላት በበኩላቸው በተባበሩት መንግስታት የልማት ፕሮግራም በእስከአሁኑ አፈፃፀም የታዩ ጥንካሬዎችን በማጎልበት፣ ድክመቶችን ለይቶ በማረምና በማስተካከል የፈፃሚ ተቋማት ሚና የጎላ መሆኑን በመግለጽ ሁላችንም የድርሻችንን እንወጣ በማለት የቢሮው ድጋፍና ክትትል ተጠናክሮ አንደሚቀጥል አሳስበዋል፡፡