አቅመ ደካሞችን አቅም በፈቀደ መጠን መደገፍ እንደሚገባ ተገለፀ
የአብክመ ገንዘብ ቢሮ በቀበሌ 3 ዲዞን ቁጠባ ሰፈር ለሚገኙ አቅመ ደካማ የማህበረሰብ ክፍሎች የመኖሪያ ቤት እድሳት ለማድረግ የቀበሌው ሊቀመንበር እና ሌሎች አካላት በተገኙበት የበጐ ተግባር ስራ መስራት ጀምሯል፡፡ የአብክመ ገንዘብ ቢሮ ኃላፊ አቶ አታላይ ጥላሁን እድሳቱን ሲያስጀምሩ አቅመ ደካሞችን አቅም በፈቀደው ሁሉ ማገዝ እንደሚያስፈልግ ገልፀው በዚህም 3 አቅመ ደካሞች ቤታቸው እንዲታደስላቸው ተጠይቀው ሙሉ ፍቃደኝነታቸውን በመግለፃቸው በአጭር ጊዜ ውስጥ ቤታቸው ተሰርቶ እንዲረከቡ እንደሚደረግ ተናግረዋል፡፡ ኃላፊው አቶ አታላይ አያይዘውም ወደፊት በትምህርት ቁሳቁስ ሌሎች ድጋፎችን ለማድረግ እንደታሰበ ጨምረው ገልፀዋል፡፡ ከአማራ ክልል ገንዘብ ቢሮ ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን ሊንኮች ይጠቀሙ ፌስቡክ https://www.facebook.com/share/191YyDU2YK/ ዩቲዩብ http://www.youtube.com/@AmharaFinanceBureau ቴሌግራም https://t.me/AmharaBureauofFinance ዋትስአፕ https://whatsapp.com/channel/0029Vb8BHKA4SpkAKHBs6M0H ኢንስታግራም https://www.instagram.com/amhara415?igsh=MTh1Nzd3dnNpaWRxMg== ቲክቶክ https://www.tiktok.com/@amhara.finance.bureau?_r=1... ዌብሳይት http://www.amharabofec.gov.com/ ኤክስ (ትዊተር) https://twitter.com/@amhara_finance