የካፒታል ፕሮጀክቶች አፈጻጸም ችግር ያለበት ስለሆነ ትኩረት ተሰጥቶበት ሊሰራ ይገባል ተባለ፡፡
የአብክመ ገንዘብ ቢሮ ከክልል ባለበጀት መስሪያቤቶች ጋር በበጀት አዘገጃጀት ፣አጠቃቀም እና የ2017 በጀት ዓመት የካፒታል ፕሮጀክቶች አፈጻጸም ዙሪያ የውይት መደረክ አካሄደ ፡፡ በውይይት መድረኩ የተገኙት የገንዘብ ቢሮ ም/ቢሮ ኃላፊ አቶ አታለይ ጥላሁን በጀት አስተዳደር ማለት ያለውን ውስን ሃብት ስራ እና በጀትን አጣጥሞ በእቅድ በመጠቀም መምራት ነው ያሉ ሲሆን የመደበኛ በጀት (የመንግስት ትሬዠሪ) ፣የእርዳታና ብድር ሃብት ፣የሲቪል ማህበረሰብ እና ሌሎች የበጀት ምንጮችን በማቀናጀት ሁሉም ተቋምት በአግባቡና ለታለመለት ዓላማ በማዋል የህዝብን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ አስቦመስራት ይገባል ብለዋል፡፡ የካፒታል ፕሮጀክት አፈጻጸማችን ከሪፖርቱ እንደተረዳነው ዝቅተኛ መሆኑ ሊያሳስበን ይገባል ያሉት ም/ቢሮ ኃላፊው አቶ አታላይ ሁላችንም በዚህ መድረክ በተስማመነው ልክ ከችግራችን ፈጥነን በመውጣት በፕሮጀክቶቻችን አፈጻጸም ላይ የሚስተዋሉ ድክመቶችን በመቅረፍ ለቀጣይ ውጤታማና ከችግር የወጣ አፈጻጸም ሊኖረን ይገባል ብለዋል፡፡ የቆሙ ፕሮጀክቶች በፍጥነት ወደ ስራ ማስገባት ይገባል ያሉት አቶ አታላይ ጥላሁን ገንዘብ ቢሮን ጨምሮ ፍትህ እና ፕላንና ልማት ቢሮ በቅንጅት በመስራት የተመደበውን የፕሮጀክት ማስፈጸሚያ በጀት በወቅቱና ለታለመለት ዓላማ ብቻ እንዲውል በማድረግ የበኩላችንን ድርሻ እንወጣ ሲሉ አሳስበዋል፡፡ በአጠቃላይ መደበኛ በጀት ከፊዚካል ስራዎቻችን ጋር አጣጥሞ እየገመገሙ መምራት እንደሚገባም ም/ቢሮ ኃላፊው ጨምረው ገልጸዋል፡፡ የአብክመ ገንዘብ ቢሮ ም/ቢሮ ኃላፊ አቶ አደራጀው ካሴ በበኩላቸው ሁሉንም ስራዎችን በፀጥታ ችግር ብቻ መሸፈን ስለሌለበት የካፒታል ስራዎቻችን የአፈጻጸም ችግር ከዚህ መድረክ መልስ በመገምገምና ቅንጅታዊ አሰራርን በማጠናከር ትኩረት ሰጥቶ ውጤት ለማምጣት መስራት ይገባል ብለዋል ፡፡ ፕሮጀክቶች በወቅቱ ወደ ስራ ገብተው ተግባራዊ ካልሆኑ አገር አይለወጥም ያሉት የመደረኩ ተሳታፊዎች በክልላችን ዛሬም ድረስ ንፁህ የመጠጥ ውሃ ችግር ፣በዳስ ትምህርት ቤቶች የሚማሩበት፣የገጠር ጠጠር መንገድ ተደራሽነት ችግር እና መሰል ችግሮች ያሉብን መሆኑን በመገንዘብ በዚህ ልክ አስበን የፕሮጀክቶቻችንን የአፈጻጸም ችግር እየቀረፉ መምራት ይጋባል ብለዋል፡፡