NEWS DETAIL

News on 'በአማራ ክልል የህዝቡን የልማት ጥያቄዎች ለመመለስ የተመደበው በጀት ለታለመለት አላማ እንዲውል…'

በአማራ ክልል የህዝቡን የልማት ጥያቄዎች ለመመለስ የተመደበው በጀት ለታለመለት አላማ እንዲውል ቁጥጥር እየተደረገ ነው

በአማራ ክልል የህዝቡን የልማት ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት የተመደበው በጀት ለታለመለት ዓላማ እንዲውል የተጠናከረ ክትትል፣ ቁጥጥርና ድጋፍ እየተደረገ መሆኑን የክልሉ ገንዘብ ቢሮ አስታወቀ፡፡ ቢሮው የ2017 ዓ.ም የስድስት ወራት እቅድ አፈጻጸም ግምገማ መድረክ በደሴ ከተማ እያካሄደ ነው፡፡ በመድረኩ የቢሮው ኃላፊ ጥላሁን መሃሪ(ዶ/ር) እንደገለጹት በበጀት ዓመቱ የህዝቡን የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት ከ150 ቢሊዮን ብር በላይ በጀት በምክር ቤቱ በማጸደቅ ወደ ሥራ ተገብቷል፡፡ የተመደበው በጀት ለታለመለት ዓላማ ጥቅም ላይ እንዲውል የተጠናከረ ክትትል፣ ቁጥጥርና ድጋፍ እያደረገ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ በክትትልና ቁጥጥሩም ባለፉት ዓመታት በበጀት አጠቃቀም ዙሪያ ይሰተዋሉ የነበሩ ችግሮች መሻሻላቸውን ተናግረዋል፡፡ ከተመደበው በጀት እስካሁን ከ32 ቢሊዮን ብር በላይ ጥቅም ላይ መዋሉን የተናገሩት የቢሮ ኃላፊው በክልሉ 79 በመቶ ውዝፍ የኦዲት ግኝትም እንዲመለስ መደረጉን ገልጸዋል፡፡ በመድረኩ የክልል፣ የዞንና የወረዳ አመራር አባላትን ጨምሮ ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል፡፡

Recent Posts

# በሶስት ክልሎች ተግባራዊ የሚሆን የ33 ሚ…
Feb. 19, 2025
የአማራ ክልል ገንዘብ ቢሮ ከፕሮጀክቶች ከዕቅድ…
Feb. 19, 2025
የካፒታል ፕሮጀክቶች አፈጻጸም ችግር ያለበት ስ…
Feb. 5, 2025
የኦዲት ግኝት ያለባቸው ተቋማት እርምት እንዲወ…
Feb. 5, 2025
ተቋማት በኦዲት የተገኘባቸውን ጉድለት እንዲያር…
Feb. 5, 2025
የእርዳታና ብድር ሃብት አጠቃቀም ትኩረት ተሰ…
Feb. 5, 2025
በአማራ ክልል በጦርነቱ ምክንያት እየደረሰ ያለ…
Feb. 5, 2025
የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች በክልሉ በሰው ሰራ…
Feb. 5, 2025
የሙስና ትግሉ የሁሉንም ህብረተሰብ ርብርብ እን…
Feb. 5, 2025
ሰብዓዊ ድጋፍ ሰጭ ድርጅቶች በአማራ ክልል ለደ…
Feb. 5, 2025
በእርዳታና ብድር የሚመጣን ሃብት ለታለመለት አ…
Feb. 5, 2025
በፈፃሚ ተቋማት ላይ የተጠያቂነት ስርዓት ተግባ…
Feb. 5, 2025
ችግሮችን የሚፈታና በእውቀት ላይ የተመሰረተ ስ…
Feb. 5, 2025
የአማራ ክልል ምክር ቤት የተቋማትን ፋይናንስ …
Feb. 5, 2025
የአማራ ክልል ገንዘብ ቢሮ ለክልል ም/ቤት ቋሚ…
Feb. 5, 2025
በአማራ ክልል የሰብዓዊ ድጋፍና ሌሎች አቅርቦቶ…
Feb. 5, 2025
#ቢሮው የ2017 በጀት ዓመት የእቅድ ኦረንቴሽ…
Feb. 5, 2025
The 2017 budget program has s…
June 19, 2024